ክፍለ ጊዜ 7
እግዚአብሔር ለእሱ እንድንኖር በምናደርገው ትግል ውስጥ ውጤታማ መሣሪያዎችን ይሰጠናል። እነሱን ሳንጠቀም ሊሳካልን አይችልም።
ሕይወት ውስብስብ ናት። ክርስትና እርስዎ ጉዳት እንዳይደርስብዎ በመደበቅ የሚጠብቅዎ እምነት አይደለም። ይልቁንም እግዚአብሔር በልባችን ውስጥ እሳትን በማስነሳት እኛ በተወለድንበት ጨለማ ውስጥ ያንን ነበልባል እንድንገልጥ ነግሮናል። እውነተኛ ሕይወታችንን የምንኖረው ዓለም ከእኛ ከሚጠብቀው በተለየ ሁኔታ እንደሆነ ይነግረናል።
ዳግም ስንወለድ ለቀሪው ሕይወታችን ቋሚ ምግብ ያስፈልገናል። በቀን በተደጋጋሚ ጊዜያት እንመገባለን። በቀን ለብዙ ሰዓታት እንተኛለን። በቀን ብዙ ውኃ እንጠጣለን። የምግብ፣ ውኃ፣ እና እንቅልፍ መንፈሳዊ አቻዎቻቸው መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ፣ መጸለይ፣ እና ከሌሎች ጋር በመሆን እሱን ማምለክ ናቸው።
ዓለም ቆሻሻ ናት። ንጹሕ እንድንሆን ይጠበቅብናል። ስንኖር በየቀኑ በልባችን ላይ ቆሻሻ እንዲጣል እናደርጋለን። በዐይናችን ብልግናን እናያለን። በጆሯችን ስድብ እንሰማለን። በእጃችን የእሾህ ሕመም እና የጓደኛን ቡጢ እንቀምሳለን። በምላሳችን መራራ መርዝ እንቀምሳለን። በአፍንጫችን የሞት ክርፋት እናሸታለን።
እግዚአብሔር ቆሻሻውን የምናጸዳበት፣ ጨለማውን ወደ ኋላ የምንገፋበት፣ እና በዙርያችን ያለውን ዓለም የምንቀይርበት ምን መሣርያዎች ይሰጠናል?
አንደኛ፣ ቀደም ሲል እንደተወያየነው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለሕይወታችን ያለውን ዕቅድ ገልጧል። የመፅሐፍ ቅዱስ ጽሑፍ በማንበብ እና በውስጡ ያሉትን የእግዚአብሔር ቃል ኪዳኖችን በማክበር አእምሯችንን እናነጻለን እንዲሁም ልባችንን እናጸናለን።
ሁለተኛ፣ ወደ እግዚአብሔር እንድንጸልይ እና ምላሽ ሲሰጠን እንዲታወቀን በውስጣችን ቅዱስ መንፈስን አኑሯል። ይህ ጽኑ እምነታችን ጥልቅ እንዲሆን ያደርጋል እንዲሁም በልዩ እንድንኖርና ዓለም እንዲቀየር እንድናግዝ ኃይል ይሰጠናል።
ሦስተኛ፣ ለአምልኮ ነው የፈጠረን። ስናመልከው ምኞታችንን ያሟላል፣ እንዲሁም ይህ ዓለም የሚሰጠንን ቁስሎችን መፈወስ ይጀምራል።
አራተኛ፣ ሰዎችን፣ እንስሳትን፣ እና ድንበር አበጅቶ የሰጠንን ዓለም እንድንወድ እና በእነሱ እንድንደሰት ፈጥሮናል። ከሌሎች ሰዎች ጋር በመሆን እና በተፈጥሮ ዓለም ለመደሰት ቅድሚያ መስጠት ያስፈልገናል።
በእግዚአብሔር ከሚያምኑ እና በምንወደው መንገድ ከሚወዱት ሌሎች ሰዎች ጋር ለመሆን ቅድሚያ መስጠት አለብን። ይህ ያበረታታናል ያጸናናል። ሚዛን እንዳንስት ይጠብቀናል። ይህ ቤተ ክርስትያን ይባላል። ቤተ ክርስትያን የምንሰበሰብበት ወይም አገልግሎት የምንካፈልበት ህንጻ አይደለም፤ ቤተ ክርስትያን እግዚአብሔርንና እኛን የሚወዱ ሰዎች ናቸው። እግዚአብሔርን ከሚወዱ ሌሎች ሰዎች ጋር ጊዜን ማሳለፍ (መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ፣ መጸለይ፣ ማምለክ፣ እና መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዴት መኖር እንዳለብን የነገረንን እንድንኖር እርስ በራሳችን መረዳዳት) ወሳኝ ነው።
ከሌሎች ክርስትያኖች ጋር መሰብሰብ አስፈላጊ ስለመሆኑ ብዙዎች አስበውበታል። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ያ ነው ዋናው ቁም ነገሩ ይላል። ኢየሱስ እንደገና የተነሳው በእሱ የሚነጻ እና በእሱ የሚረካ ማሕበረሰብን ለመገንባት ነው። ይህንን ከሞት ከተነሳ በኋላ ከጓደኞቹ ጋር ሲመገብ፣ ከእነሱ ጋር ሲራመድ፣ እና በግል ክፍላቸው ሲጎበኛቸው ባሳየው ባህርይ በምሳሌ አስረድቷል።
ያ ለእኛ በቂ ካልሆነ ይህ አንድ ቄስ የነገረን ቀስቃሽ ታሪክ ሊያግዝ ይችላል፡-
አንድ ቀን አንድ ሰው ወደ አንድ ቄስ ይመጣና "አባ፣ ወንድሜ ጳውሎስ እራሱን ከእኔ እና ከሌሎች ክርስትያኖች ሁሉ ጋር አቆራርጧል። እርስዎ ሊያነጋግሩት እና መመለስ እንዳለበት ሊያሳምኑት ይገባል!" አላቸው።
ቄሱ ወደ ጳውሎስ ቤት በመሄድ ያንኳኩና እንዲገቡ ተነገራቸው።
ከገቡ በኋላ፣ ጳውሎስን የሚንቀለቀል እሳት ላይ አፍጥጦ ያገኙታል። አንገታቸውን በመነቅነቅ ድምጽ አልባ ሰላምታ ተለዋወጡና ቄሱ ከጳውሎስ ጎን ተቀምጠው እሳቱ ላይ ያፈጣሉ። ከአፍታ በኋላ፣ የብረት መቆንጠጫዎች ያነሱና ከእሳቱ ፍም ከሰል አንስተው ከእሳቱ ውጪ ያለው ድንጋያማ መሬት ላይ ያስቀምጡታል። ለጳውሎስ አንገታቸውን በመነቅነቅ ፈገግ ብለው ጠበቁት። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ፣ ከሰሉ በጣም ቀዝቅዞ ምንም የቀረ እሳት አልነበረውም።
ቄሱ ለጳውሎስ አንገታቸውን በመነቅነቅ ከሰሉን አንስተው ወደ እሳቱ መልሰው ይወረውሩታል። ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከሰሉ እንደገና ይነድ ነበር። ቄሱ ስቀው፣ ጳውሎስ ላይ አንገታቸውን ነቀነቁ እና ለመሄድ ተነሱ።
ያ ከሰል እኛ ነን። በዙርያችን ያሉ ሌሎች ሰዎች የሚያነዱት እሳት ሳይኖር በመጨረሻ ቀዝቅዘን እሳታችንን እናጣለን። መጽሐፍ ቅዱሳችንን ማንበብ፣ ዕለታዊ የጸሎት እና የአምልኮ ጽኑ ልማድ ማዳበር፣ እና እግዚአብሔርን በደስታ እየታዘዝን እንድንኖር እርስ በራሳችን እንድንተጋገዝ ከሌሎች ክርስትኖች ጋር ጊዜ ለማሳለፍ ቅድሚያ መስጠት አለብን።
ይህንን ካደረግን እግዚአብሔር ያጸናናል፣ ያበረታታናል፣ እና ይባርከናል። ከዚያ ወንጌልን እንደ እኛ አጥብቆ ከሚያስፈልጋቸው ሰዎች ጋር እንድንካፈል ዕድሎችን ይሰጠናል።
ጠለቅ ይበሉ
ገላትያ 5:22-26፣ መዝሙር 121:1-8 እና 1ኛ ቆሮንቶስ 12:20 - 13:13ን ያንብቡ። እግዚአብሔር እንድንኖር የሚፈልገው እንዴት እንደሆነ ግልጽ ሆኖሎታል? በእነዚህ ጥቅሶች ስላነበቡት ፍቅር እንዲኖሩ ጽናት እንዲሰጥዎት ለእግዚአብሔር ይጸልዩ። ይህን ዓይነቱን ፍቅርን በተግባር ማሳየት የሚችሉበት አንዱ መንገድ ምንድን ነው? ይጻፉትና ከዚያ ሄደው ይተግብሩት!