ክፍለ ጊዜ 1

የምስራች አለን፡፡ ለእግዚአብሔር በፍቅር እስከታመንን እና እስከተገዛን ድረስ ሊወደንና ይቅርታ ሊያደርግልን፣ ዘለዓለማዊ ህይወት ሊሰጠን፣ ከክፋት ነፃ ሊያደርገን እና ወዳጆቹ ሊያደርገን ቃል ገብቷል፡፡

እርስዎ ይህንን ያምናሉ? ይህ ለርስዎ ምን ማለት እንደሆነ ይረዱታል?

መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን የተወለድነው እግዚአብሔርን ለዘለዓለም ልንወደው፣ ልንገዛለት፣ እና ልንደሰትበት ነበር፣ ግን አንችልም፡፡

ለምን?

ምክንያቱም በሁለት መንገድ ከእሱ ተነጥለን ስለተወለድን ነው።

በመጀመርያ ደረጃ፣ እሱን አናውቀውም፣ የማናውቀውን ሰው መውደድ ደግሞ አንችልም።

በሁለተኛ ደረጃ፣ የተወለድነው ከእግዚአብሔር ህይወት፣ እውቀት፣ እና ፍቅር ከሚነጥሉን ክፉ ምኞቶች ጋር ነው። ለሞት፣ ለሕመም፣ ለኢፍትሐዊነት፣ ለጦርነት፣ እና ለህይወት መከራዎች ሁሉ መንስኤ ናቸው።

ክፉ ምኞቶቻችን ከእግዚአብሔር የሚነጥሉን እንዴት ነው?

የክፋት ዋነኛው መንስኤ ወዳጅነቶችን የሚጎዳ ራስ ወዳድነት ነው። አንድ ሰው ከሚስቱ ጋር በተወዳጀ ቁጥር ቃሉ፣ ተግባሩ፣ እና ሀሳቡ እሷን ምን ያህል ሊያስቀይማት እንደሚችል በቀላሉ ይገነዘባል። ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ወዳጅነትም እንዲሁ ነው። ወደ እግዚአብሔር በቀረብን ቁጥር ክፋታችን ከእሱ ጋር ያለንን ቅርበት እንዴት እንደሚያበላሽ የበለጠ እንረዳለን።

ከእሱ ለመነጠላችን የእግዚአብሔር ምላሽ ምን ነበር?

እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ጥብቅ ወዳጅነትን ለማደስ ሰው ለመሆን መረጠ፡፡ ያ ሰው ኢየሱስ ነበር።

እግዚአብሔር ሰው መሆን ያስፈለገው ለምንድን ነው?

መጀመሪያ፣ ከእኛ ጋር በየግል ለመገናኘት፡፡ ሁለተኛ፣ ደስታችንን፣ ሕመማችንን እና ትግላችንን ለመቅመስ። ሦስተኛ፣ በእኛ ምትክ በመሞት የክፋታችንን ቅጣት ለመሸከም። እና አራተኛ፣ ክፋታችንን ለማጠብ ከሞት ለመነሳት፤ በዚህም ከእርሱ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት እንዲኖረን እና ዘለአለማዊ ሕይወት እንዲሰጠን።

ኢየሱስ ለእኛ መሞት የመረጠው በከፊል እግዚአብሔር ክፋትን እንደሚቀጣ ለማረጋገጥ ነው። ክፋትን ሳይቀጣ የሚተው እግዚአብሔርን አንፈልግም። የኢየሱስ ሞት እግዚአብሔር ይህንን እንደማያደርግ ዋስትና ነው፣ ምክንያቱም እሱ ስህተት በጭራሽ ፈጽሞ ባያውቅም ስለ ክፋታችን እራሱን ለመቅጣት መረጠ።

የነበረው ታላቅ ዓላማ ከእሱ ጋር በንጹሕ ወዳጅነት መኖር እንድንችል ከክፉ ምኞታችን ነጻ ለማውጣት እና ልባችንን ለመቀየር ነበር። ይህንን ነው መጽሐፍ ቅዱስ “እንደገና መወለድ” ብሎ የሚጠራው። ሙሉ በሙሉ መቀየር፣ ከክፉ ምኞታችን ባርነት ነጻ ሆነን መኖር፣ ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ወዳጅ መሆን ማለት ነው።

ያ ማለት የምስራቹ ኢየሱስ ቅጣታችንን መውሰዱ ላይ አያቆምም።

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ከሙታን ተነስቷል እና አሁንም በሕይወት አለ ይላል። የሕይወት መቀያየር ሰጥቶናል፡- የእሱን ፍጹማዊ ሕይወት ለእኛ ለተሰበረው ሕይወት። ይህንን አስደናቂ ስጦታ ስንቀበል መንፈሱ በእኛ ውስጥ መኖር ይጀምራል እናም ቀስ በቀስ ክፉ ምኞቶቻችንን በእሱ ቸርነት ይተካል።

የምንነጻበት እና ፍጹም የምንሆንበት ሂደት ቅድስና ተብሎ ይጠራል። ይህ ሕይወት እስከሚያበቃ ድረስ ፍጹም አይደለንም። ሆኖም ግን፣ ሂደቱ ተግባራዊ ውጤት ወዲያው ይሰጣል።

እነዚያ ውጤቶች የመንፈሱ ፍሬዎች ይባላሉ፡- ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግስት፣ ቸርነት፣ መልካምነት፣ ታማኝነት እና ራስን መግዛት። ክርስትያን ከሆንን በእነዚህ ባህርያት እናድጋለን። ካልሆንን ደግሞ እራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን የምንሰጥበት እና መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ፣ ከክፋት በመዞር፣ በመጸለይ፣ እና እሱን በማምለክ ወደ እሱ የምንቀርብበት ጊዜ ይህ ነው።

የመንፈሱ ፍሬ እንዲያድግ ማድረግ አንችልም። እኛ ፍቅራችንን ለክርስቶስ ስንገልጽ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ይችላል።

መጽሐፍ ቅዱስ መስቀላችንን ልናነሳና ኢየሱስን ልንከተለው ያስፈልገናል ይላል። ያ ሐረግ የራስ ወዳድነታችን ሞትን የሚወክል ተምሳሌት ነው። ኢየሱስ የራሱን መስቀል (ማሰቃያ መሳሪያ!) እንደተሸከመው እና እዛ ላይ ተሰቅሎ እንደሞተ ሁሉ እኛም በራስ ወዳድነታችን ሞት አማካኝነት በተምሳሌት አንደዛ ማድረግ አለብን።

ይህ ለምን ያስፈልጋል? ምክንያቱም የእኛ ራስ ወዳድ ምኞቶች ከእግዚአብሔር ምኞቶች ጋር ጦርነት ላይ ናቸው። ኢየሱስ ራስን ሙሉ ለሙሉ ለእሱ መስጠትንና እምነትን ይፈልጋል። ራስ ወዳድ ምኞቶቻችንን በእግዚአብሔር ምኞት እንድንቀይር ይጠይቃል። ይህ እግዚአብሔርን እና ሕዝቦቹን በትሕትና በማገልገል ፍቅራችንን ለማሳየት ነው።

እራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ እና እንደ ብቸኛ ደስታ እሱን ስንመርጥ እሱን ለመታዘዝ ብርታቱንና ምኞቱን ይሰጠናል። እሱ እንደ ምንተነፍሰው አየር እንዲሆን እንደመፍቀድ ነው። ኢየሱስን ወደ ውስጥ ይተንፍሱት። ኢየሱስን ወደ ውጭ ይተንፍሱት። ይድገሙት። በየቀኑ። እስከ እለት ሞታችን ድረስ። ይህን ማድረግ እሱ ጠላቶቻችንን በፍቅር እንድንይዝ ሲያዝዘን እንድናደርገው የሚረዳን መሆኑን ለማመን ድፍረት የሚሰጠን ይህ ነው።

ከኢየሱስ ጋር ያለን ግንኙነት የሱ መንፈስ በእኛ ወስጥ ስላለ በተግባር ልንኖረው የምንችለው እጅግ ጥብቁ ግንኙነት ነው። ይህ ግንኙነት እግዚአብሔርን በፍቅር ሲያምኑት እና ሲታዘዙት ሕይወትዎን ቀይራል። ከዚያ እርስዎ ስህተት ሲፈጽሙ እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ እንድታደርጉት ይረዳዎታል።

ይህ አይነት ሕይወት መደበኛ ሕይወትን ከማጣጣም ሊያግድኝ ይችል ይሆን ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ። እግዚአብሔርን መውደድ እና ለሱ መታዘዝ የእግዚአብሔርን ሰላምና ደስታ በሕይወት እንድናጣጥም ያስቻለን መሆኑ ስናሳውቅዎ በደስታ ነው።

በዚህ ሕይወት ከክፉ ምኞቶች ሙሉ በሙሉ በፍፁም ነጻ ባንሆንም አሁንም ስሕተት ብንፈጽምም ክፉ ምኞቶቻችን አቅማቸውን እንዲያጡ ለኢየሱስ ያለን ፍቅር እነሱን ያስርባቸዋል። እግዚአብሔር ይህን የሚያደርገው እሱን፣ ዓለምን፣ እና በንጽሕና የሰጠንን ግንኙነቶችንን እንድናጣጥም ነጻ እንድንሆን ነው።

ብዙዎቻችን ለማመን አስቸጋሪ ሆኖ የምናገኘው ቃል ኪዳን እግዚአብሔር ምኞቶቻችንን ይቀይራል የሚለውን ነው። እርሱ ያደርገዋል። እውነት ነው። ካልሆነ፣ የምስራቹ መልካም ዜና ባልሆነ ነበር።

ለምንድን ነው ብዙ ክርስትያኖች መልካም ሕይወት የማይኖሩት?

እያንዳንዱ ክርስትያን ከክፋት ነጻ ሆኖ መኖር ይችል ነበር፣ ይሁንና ይህን ለማድረግ ፈቃደኛ የማንሆንባቸው ጊዜያት አሉ። አንዳንድ ጊዜ ክርስትያን ከሆንም በኋላ ከኢየሱስ ይልቅ ክፋትን እንመርጣለን።

አንዳንዶች ከክፋት ነጻ ሆነው እንዳይኖሩ የተያዙ አሉ ምክንያቱም ይህ ነጻነት እንደሚቻል ወይም እግዚአብሔር ይሰጣል ብለው አያምኑም። ሌሎች ብዙ ዋጋ ስለሚያስከፍል ከክፋት ነጻ ሆነው ለመኖር ፈቃደኛ አይደሉም። ምክንያቱም ይህ አጠቃላይ የሆነ፣ ቀጣይነት ያለው ራስን ለእግዚአብሔር አሳልፎ መስጠትን ስለሚጠይቅ ነው።

ይህ ምን ማለት ነው?

እራሳችንን ለእግዚአብሔር አሳልፈን ከሰጠን በኋላ ራሳችንን መስጠት እንድንቀጥል እንታዘዛለን። ሁላቸንም ወደ ራስ ወዳድነት የመመለስ አዝማሚያ ስላለን ይህ በቋሚነት መከናወን አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ዝንባሌ የኃጥያት ተፈጥሮ ይለዋል። ይህ እኛ ከተወለድንበት ቀን እስከ ዕለተ ሞታችን ድረስ አለን።

እግዚአብሔርን ስናምን፣ ከክፋት ስንመለስ፣ ስንጸልይ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ፣ እና ከሌሎች ክርስትያኖች ጋር ስንሰበሰብ በውስጣችን ያለው የክርስቶስ መንፈስ ምኞቶቻችንን መለወጥ ይጀምራል እንዲሁም ከኃጥያት ተፈጥሮ በየጊዜው የሚጨምር ነጻነት ይሰጠናል።

ዕድገት ጊዜ ይወስዳል። በሂደቱ ውስጥ ተስፋ አይቁረጡ። የዕድገቱን አዝጋሚ መሆን በጭራሽ ላለማደግ እንደ ምክንያት አይጠቀሙበት።

እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ ማድረግ በዚህ ዓለም የማይገኝ ዘላቂ ደስታ እና ሰላምን ያመጣል። ከክፋት የምንመለሰው ክፋት እንዲሁ መጥፎ ስለሆነ አይደለም፤ ከክፋት የምንመለሰው በእግዚአብሔር ለመደሰት ነው።

እግዚአብሔር ከእሱ ጋር እንድንሆን የሚጠራን ለክብሩ በመስራት እንድንኖር ነው። እራሳችንን ለእሱ አሳልፈን ከሰጠን በኋላ ወንጌላዊነት ተብሎ የሚጠራውን ከሌሎች ጋር የሚኖር መልካም ግንኙነትን ለሌሎች እንድናጋራ እና ደቀመዝሙርነት ተብሎ የሚጠራው እንዴት እደሚኖሩት እንድናስተምራቸው ያነሳሳናል።

እርሱ የሚሰጠን ነገር እጅግ መልካም በመሆኑ ስንኖረው ስለእርሱ ከማጋራት ወደኋላ ማለት አንችልም። አንድ ጊዜ ጌታ መልካም መሆኑን ከቀመስንና ካየን፣ የተሰጠንን ነጻነት እና ደስታ ሰዎችም እዲሰማቸው በተፈጥሮ ለሰዎች ልንነግራቸው እንፈልጋለን።

እንደገና፣ ይኸው የምስራች (እጅግ ምርጥ የምስራች!)፡- ለእግዚአብሔር በፍቅር እስከታመንን እና እስከታዘዝን ድረስ ሊወደንና ይቅርታ ሊያደርግልን፣ ዘለዓለማዊ ህይወት ሊሰጠን፣ ከክፋት ነፃ ሊያደርገን እና ከእርሱ ጋር ጥብቅ ወዳጆች ሊያደርገን ቃል ገብቷል። እስከ ሕይወታችን መጨረሻ ድረስ ለእርሱ ታማኝ ከሆንን ከእግዚአብሔር ጋር ለዘለአለም እንድንኖር ሙሉ በሙሉ ከክፋት ምኞቶች እርግማን፣ ከሞት እና ከመንፈስ ስብራት ነጻ የሆነ አዲስ ሰውነት ሊሰጠን ቃል ይገባል።

መጥፎው ዜና የሆነው የእግዚአብሔር ስጦታን ያልተቀበለ ሁሉ ሁላችንም በክፋታችን ያገኘነውን ማለቂያ የሌለው ቅጣት እና ከእግዚአብሔር መነጠል ይደርስብናል የሚል ነው።

የእግዚአብሔር የምስራች እና እርሱን ሳንቀበለው ስንቀር የሚከሰተው መጥፎ ዜና ወንጌልን በሕይወታችን ውስጥ እጅግ ጠቃሚ እውነታ ያደርጉታል።

የምንኖረው እግዚአብሔርን ለዘለአለም ለማክበር እና በእሱ ለመደሰት ነው። ብዙ ጊዜ እራሳችንን በማስደሰት እና እግዚአብሔርን በማስደሰት መካከል መምረጥ እንዳለብን እናስባለን። እውነታው ግን ለክፉ ምኞቶቻችን መንበርከክ ለረዥም ጊዜ አያስደስተንም። በክፋት መዘፈቅ ለድባቴ፣ ለራስ የሚሰጥ ዋጋ ማነስ፣ እና ለአፍራሽ ክፉ ባህርያት ሱስ ይዳርጋል። ክፋት ይገዛናል፣ ደስታችንን ያደማል፣ ባዶና ብቸኛ አድርጎ ይተወናል። ባርያዎች ያደርገናል።

እራሳችንን የክፋት ባሪያ ከመሆን ይልቅ የእግዚአብሔር ቸርነት ፈቃደኛ አገልጋዮች አድርገን ለመመልከት ስንመርጥ በሕይወታችን ውስጥ የእግዚአብሔር መገኘት እና እርሱ በወንጌል ውስጥ ቃል የገባልን ታላቅ ስጦታዎች ምንም ነገር ሊወስድብን የማይችላቸውን ደስታ እና ነጻነት ይሰጠናል።

የሚያስፈልገው ሁሉም ነገር ነው፡፡ ኃጥያታችንን ሁሉ ይቅር ብሎናል፣ ሕይወት ሰጥቶናል እንዲሁም ፍቅራዊ ደግነቱን አሳይቶናል።

ይህንን ለማስታወስ ቀላሉ መንገድ በመዳን ግጥም ነው፡-

ኢየሱስ በመስቀል ሞተሃል
ተነስተሃል ልታድነኝ
ይቅር በለኝ ሁሉ ሃጢያቴን
ሁን ወዳጄ ጌታዬ አዳኜ
ህይወቴን ለውጥ አዲስ አርገው
እርዳኝ ጌታ ለአንተ እንድኖር

ጠለቅ ይበሉ

ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በቀጥታ ለእርስዎ እና ለእኔ የጸለየውን ጸሎት የተመዘገበበት ዮሐንስ ምዕራፍ 17ን ያንብቡ። ኢየሱስ ስላለው ነገር ደስ የሚሉ ዝርዝሮች ሆነው ያገኟቸውን ነገሮች ለመጻፍ ይሞክሩ፣ ከዚያ ያንብቡ እና ጥያቄዎችዎን ከሌላ ክርስትያን ጋር በመሆን ይወያዩ። በግል ደረጃ፣ ኢየሱስ ለእርስዎ መጸለዩን በተመለከተ ምን ያስባሉ?

ያለፈው ዝርዝር ዝርዝር ቀጣይ

This website uses cookies to ensure you get the best experience on our website.

By continuing to use this site, you agree to our use of cookies.