ክፍለ ጊዜ 8

መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እሱ ማን እንደሆነ፣ እኛ ማን እንደሆንን፣ ከየት እንደመጣን እና መኖራችን ለምን እንደሆነ የሚያብራራበት መንገድ ስለሆነ የእግዚአብሔር ቃል ተብሎ ይጠራል። ውስብስብ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችንን በዘፈቀደ አንድ ቦታ ላይ ብንገልጸው ሊምታታብን ይችላል። ይህ የሆነበት ምክንያት መጽሐፍ ቅዱስ ባለፉት 2000 ዓመታት ገደማ በተለያዩ ጸሐፊዎች የተጻፉ የተለያዩ 66 መጽሐፍቶችን የያዘ ነው።

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው። ከዚያ ባሻገር እግዚአብሔር የመጻሕፍቱ ይዘቶች እውነት እና ከእሱ እንደሆኑ አረጋግጧል። ብዙዎቹ መጻሕፍት የተዘጋጁት ለተወሰኑ የሕዝብ ቡድኖች ነበር። የጥንቷ ቤተ ክርስትያን እነዚህን መጻሕፍት በአንድ ቅጽ አሰባስባ አሁን መጽሐፍ ቅዱስ ብለን የምንጠራውን መጽሐፍ አዘጋጅታለች። በአንድ ላይ፣ እግዚአብሔር በታሪክ ለዘመናት እንዴት ከሰው ልጅ ጋር እንደተገናኘ ያሳያሉ።

የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት የተጻፉት በተለያዩ ዘውጎች ነው። ለምሳሌ መጽሐፈ መዝሙር የመዝሙር እና የጸሎት መጽሐፍ ነው። ሁልጊዜ ቃል በቃል መወሰድ በሌለባቸው ሰውኛ ዘይቤዎች የተሞላ ነው። የዮሐንስ ወንጌል ግን በኢየሱስ ሕይወት ላይ የተመሰረተ ታሪካዊ ጽሑፍ ነው።

መልእክቶች፣ እንደ ገላትያ እና ኤፌሶን መልእክቶች ያሉት፣ የጥንት የቤተ ክርስትያን መሪዎች ለተወሰኑ የሕዝብ ቡድናች የጻፏቸው ደብዳቤዎች ነበሩ።

በመጀመሪያ ለጥንት የክርስትያን ቤተ ክርስትያን እንደተጻፈው ረጅም እና ውስብስብ ትንቢት የሆኑ እንደ ኢሳይያስ እና የራዕይ መጽሐፍ ያሉ የትንቢት መጻሕፍት አሉ።

ተጨማሪ አለ፣ ግን ሐሳቡ ገብቷችኋል

በተጨማሪ መጽሐፍ ቅዱስ በሁለት ኪዳናት የተከፈለ ነው። ብሉይ ኪዳን ከኢየሱስ ልደት በፊት የተጻፉ መጻሕፍትን የያዘ ሲሆን ሐዲስ ኪዳን ከኢየሱስ ልደት በኋላ የተጻፉ መጻሕፍትን የያዘ ነው።

የመጀመሪያዎቹ አምስት የመጽሐፍ ቅዱስ መጻሕፍት (የኦሪት መጻሕፍት) የተጻፉት በእስራኤላውያን ለእስራኤላውያን ሲሆን ስለ ዓለም መጀመሪያ፣ እግዚአብሔር ለእስራኤላውያን የሰጣቸውን ቃል ኪዳኖች እንዲሁም እስራኤላውያንን እንዴት እንደ ብሔር እንዳቋቋማቸው ያብራራሉ።

በመላው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በእግዚአብሔር እና በሰዎች መካከል የተለያዩ ስምምነቶች አሉ። እነዚህ ቃል ኪዳን ተብለው ይጠራሉ። ዛሬ የምንኖረው በኢየሱስ ቃል ኪዳን ስር ነው። ያ ማለት እንደ ዘሌዋውያን ወይም ዘዳግም ባሉ መጻሕፍት ውስጥ የተዘረዘሩትን እግዚአብሔር ከአይሁድ ህዝብ ጋር በገባው ጥንታዊ ቃል ኪዳን ስር የነበሩትን ስነ ስርዓታዊ ህጎች መከተል አይጠበቅብንም ማለት ነው። እነዚህ ስነ ስርዓታዊ ሕጎች ኢየሱስን የሚያመለክቱ ምሳሌዎች ሲሆኑ ስነ ስርዓታዊ ሕጎቹ በእርሱ ሕይወት እና ሞት ተጠናቀዋል።

ጭንቅላትዎን ከዞረብዎት፣ አፍታ ወስደው ትንፋሽ ይውሰዱ። ከዚያ ይበረታቱ ምክንያቱም ሁሉንም ነገር አሁንኑ መረዳት የለብዎትም!

መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ግዴታ ማንበብ ያለብዎት ነገር አይደለም። ሊያነቡት የሚገባ ነገር ነው። በሕይወት ዘመንዎ እንዲደሰቱበት፣ እንዲያነቡት፣ እንዲያጠኑት፣ እና እንዲኖሩት የተዘጋጀ ነው። አእምሮዎን እና ልብዎን የሚቀይር ውድ ሀብት ነው።

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ከሌሎቹ የበለጠ ለመረዳት ቀላል ናቸው። የዘፍጥረት መጽሐፍን (የመጽሐፍ ቅዱስ የመጀመሪያ መጽሐፍ) እና ቢያንስ ከአራቱ ወንጌሎች (ማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስ፣ ወይም ዮሐንስ) አንዱን እንዲያነቡ እንመክርዎታለን።

ከዚያ በመነሳት ወደ ዘጸአት፣ አዲስ ኪዳን ውስጥ ወደ ሚገኙ የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ እና ደብዳቤዎች መሄድ ትርጉም ሊኖረው ይችላል።

የሮሜ እና የዕብራውያን መጻሕፍት ለማንበብ አስቸጋሪ የሆኑ መጻሕፍት ናቸው፣ ሆኖም በኢየሱስ አዲስ ቃል ኪዳን እና በብሉይ ኪዳን ውስጥ ባሉ የቀድሞ ቃል ኪዳኖች መካከል ያለውን ልዩነት ለመረዳት ያግዛሉ፡፡

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ አስደናቂ ታሪኮች አሉ። የአይሁዳውያንን የዘር ሐረግ እና ለአይሁዳውያን ስለተሰጡ ውስብስብ ሕጎች የሚገልጹ ክፍሎችም አሉ። ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ እያንዳንዱ ነገር መልካም ዓላማ እንዳለው እና እኛ ማን እንደሆንን፣ እሱ ማን እንደሆነና እንዴት እንደምንኖር ለመረዳት ስለሚያግዘን መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናቱ ጠቃሚ ሰለመሆኑ እርግጠኛ መሆን ይችላሉ። ለዚህ ነው መጽሐፍ ቅዱስን እንዳያነቡ ከሚያግድዎ ማንኛውም ነገር መጠንቀቅ ያለብዎ። ስልክዎ፣ የቪዲዮ ጨዋታዎች፣ ወዘተ።

መጽሐፍ ቅዱስ ከሌልዎ አንድ ማግኘት አለብዎ።

መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉውን በአንድ ዓመት ውስጥ ለማንበብ መርሀ ግብሮች ያሉ ሲሆን ትንንሽ ክፍሎችን በየቀኑ እንዲያነቡ ስለሚያደርጉዎ አጋዥ ናቸው።

ብዙ ማንበብ ከፈለጉ ይቀጥሉ። ግን የእግዚአብሔርን ቃል ለማጣጣም መማር ላይ ማተኮር የተሻለ ነው። የመጽናናት እና የጥበብ ቋሚ ምንጭ ሲሆን የክርስትያን ሕይወት የመምራት ችሎታዎ መጽሐፍ ቅዱስን በልብዎና በአእምሮዎ እንዴት በተከታታይ እንደሚያሰላስሉት ጋር በቀጥታ የተቆራኘ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስን ለመረዳት እግዚአብሔር እንዲያግዝዎት ይጠይቁ። ትእዛዛቱን በዕለተ ተዕለት ሕይወትዎ ውስጥ ለመተግበር እንዲረዳዎ ይጠይቁት። መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማዳመጥ ችላ አይበሉ። እንዲረሱት አይፍቀዱ። አንባቢ መሆንዎን ላያስቡ ይችላሉ፣ ግን ለእርስዎ የእግዚአብሔር ቃል ስለሆነ መጽሐፍ ቅዱስ በፍጥነት እጅግ ውድ ሀብትዎ ይሆናል።

ጠለቅ ይበሉ

መጽሐፍ ቅዱስ ያግኙ፣ "መጽሐፍ ቅዱስን በአንድ ዓመት ውስጥ አንብብ" የሚል መርሐ ግብርን ይፈልጉ እና ያንን የንባብ መርሐ ግብር ይከተሉ።

ያለፈው ዝርዝር ዝርዝር ቀጣይ