ክፍለ ጊዜ 9
ጸሎት ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ነው።
ኢየሱስ ይህን የሚያሳይ ቀላል ምሳሌ በማቴዎስ 6፡9-13 ላይ የሚገኘውን "የጌታ ጸሎት" ተብሎ በሚጠራው ጸሎት ላይ ሰጥቷል። ይህ ጸሎት እንዴት መጸለይ እንዳለበት ከጓደኞቹ አንዱ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ነበር።
ሆኖም ከጓደኞች ጋር የተለያዩ የንግግር ዓይነቶች እንዳሉ ሁሉ የተለያዩ የጸሎት ዓይነቶች አሉ። ለሌሎች ሰዎች መጸለይ እንችላለን። ለራሳችን መጸለይ እንችላለን። ጥበቃን፣ ፈውስን፣ ጽናትን፣ እና ጥበብን መጠየቅ እንችላለን። እግዚአብሔርን ለቸርነቱ፣ ለምሕረቱ፣ እና ለይቅር ባይነቱ ማመስገን እንችላለን። ስለምንወደው ነገር ልንነግረው እንችላለን። ለሰጠን ነገር ማመስገን እንችላለን። ወይም ጭንቀታችንን፣ ፍርሃቶቻችንን፣ ጥርጣሬዎቻችንን፣ እና ጥያቄዎቻችንን መንገር።
ይህ ሁሉ መልካም ነው!
እግዚአብሔር ከልብ የመነጨ ጸሎት ማቅረብዎ ያስደስተዋል። ሐሳብዎትን ያውቃል። በሙሉ ልብዎ ይጸልዩ። በትሕትና፣ በምስጋና እና በልበ ሙሉነት ይቅረቡት።
እጆችዎን ከፍ አድርገው፣ በጉልበትዎ ላይ አድርገው ወይም አጣምረው ይጸልዩ። ዓይኖችዎን ከፍተው ወይም ጨፍነው ይጸልዩ። ይራመዱ፣ ይቁሙ፣ ይቀመጡ፣ ያጎንብሱ፣ ወይም ጋደም ይበሉ። ጠዋት ወይም ምሽት ወይም ከሰዓት በኋላ ላይ ወይም ቀኑን ሙሉ ይጸልዩ።
ጥልቅ ቃላትን ለመጠቀም አይሞክሩ። እግዚአብሔር በውብ ቃላት አይደነቅም። እሱ እርስዎ ከሚያውቁት በላይ ያውቃል። እውነተኛ ብቻ ይሁኑ። እራስዎን በመሆን እግዚአብሔርን በአክብሮት ያነጋግሩት። እርሱ ጸሎትዎን መስማት እንደሚፈልግ እና በእርግጥ ከእርስዎ ጋር መሆንን እንደሚወድ ይመኑ።
ለብቻዎ ይጸልዩ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ይጸልዩ። በጋራ መጸለይ ጠቃሚ ነው! አንድ ላይ ያገናኘናል ይህም እግዚአብሔርን ያስደስተዋል።
ድምጽ አውጥተው መጸለይ የበለጠ በሚመቻቸው ሌሎች ሰዎች ምክንያት ወደ ኋላ አይበሉ። ጸሎት ስለእኛ አይደለም። ጸሎት ለእግዚአብሔር የልባችንን ስንገልጽለት ወደ እሱ የበለጠ ስለመቅረብ ነው። አንድ ሰው በአጸላለይዎት ምክንያት እንዲሸማቀቁ ካደረገ፣ ያ ከእርስዎ የበለጠ ስለዛ ሰው ብዙ ይናገራል። ያ ትዕቢትን ያሳያል፣ ትዕቢት ደግሞ ክፉ ነው።
እያንዳንዱ ክርስትያን ትጉህ የጸሎት ልማድ ማዳበር አለበት። ይህ በየቀኑ ለመጸለይ የጊዜ ሰሌዳ ማውጣት ማለት ነው። ያንን ካላደረጉ ጸሎት ከሕይወትዎ የሚጠፋበት መንገድ አለው። የጊዜ ሰሌዳ ያለው ጸሎት ካላደረጉ በአስራ አምስት ደቂቃ የጊዜ ክፍፍል መጀመርን ያስቡ። የጊዜ ሰሌዳዎን ቀንዎን ከመጀመርዎ በፊት ማለዳ ላይ ቢያደርጉት ይመከራል። ይህ የጊዜ ሰሌዳዎን ማታ ላይ ሲያደርጉ ሊደክምዎ፣ ጊዜ ሊጠብዎ ወይም ሊዘናጉ ስለሚችሉ የበለጠ አጋዥ ነው። ጸሎት የቀንዎን ውሎ በአዎንታዊ መንገድ ለመለወጥ የሚያስችል መንገድ አለው።
የጸሎት ጊዜዎን በተለያየ ክፍሎች ይከፋፍሉት። ስለምን እንደሚጸልዩ ለማሰብ ከተቸገሩ የሚመለከቱት ነገር እንዲኖርዎት የጸሎት እቅድ በጽሑፍ ማስፈር አጋዥ ሆኖ ሊያገኙት ይችላሉ።
አንድ የእቅድ ሐሳብ እነሆ፡- መጀመሪያ፣ የሰሩትን ማንኛውም ጥፋት ይናዘዙና እግዚአብሔርን ይቅርታ ይጠይቁት። ከዚያ ለቸርነቱ፣ ለይቅር ባይነቱ፣ ለየዋሕነቱ፣ እና ለፍቅሩ ለማመስገን ጥቂት ደቂቃዎችን ይውሰዱ። ለታማኝነቱ እና ለኃይሉ ውዳሴ ለማቅረብ ተጨማሪ ደቂቃዎችን ይውሰዱ። ለቤተሰብዎ እና ለጓደኞችዎ ይጸልዩ። እግዚአብሔር እንዲያነጋግርዎ በመጠበቅ ለተወሰነ ጊዜ ዝም ይበሉ። ከዚያ እግዚአብሔር ለቀንዎ ብርታት እንዲሰጥዎ ለመጸለይ ቀሪውን ጊዜ ይጠቀሙበት።
መጽሐፍ ቅዱስን እንደ ጸሎት መመሪያም መጠቀም ይችላሉ። ለምሳሌ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ያንብቡ፣ ከዚያ ስላነበቡት ነገር ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገሩበት እና ግር ያልዎትን ነገር ለመረዳት እንዲያግዝዎት ይጠይቁት።
መልካም ልማዶች ለመዳበር ጊዜ ይወስዳሉ። በሂደቱ ትዕግስት ያድርጉ። እራስዎን ይታገሱ። በቃ ሰነፍ አይሁኑ።
በየቀኑ አስራ አምስት ደቂቃዎችን ጸሎት ላይ ለማሳለፍ ከተጉ በኋላ ብዙ ሰዎች የጸሎት ጊዜን ለማራዘም ይፈልጋሉ። ይህ ድንቅ ነው! ጊዜውን በተለያዩ ትኩረቶች ላይ መከፋፈል አጋዥ ሆኖ አግኝተነዋል። እንዳንጨናነቅ ወይም ተስፋ እንዳንቆርጥ ይጠብቀናል።
ጸሎት ታስቦ የሚደረግ ነው። ልክ እንደ ፍቅር፣ እውን እንዲሆን ንቁ መሆን አለበት።
ለመሞከር ከወሰኑ ለአንድ ሰዓት መጸለይ የሚቻል ብቻ ሳይሆን አስደሳች መሆኑም ሊያስገርምዎት ይችላል! ያም ጸሎት ስለሚያስፈልገን ነው። ከምንም ነገር በላይ ከእግዚአብሔር ጋር ጥብቅ ግንኙነት እንዲኖረን እንናፍቃለን። ያ የጠበቀ ግንኙነት ደግሞ እኛን ይቀይረናል።
እግዚአብሔር ለጸሎት ይጠራናል። ከእሱ ጋር እንድንነጋገር ይሻል። ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ሌላ ምንም ነገር በማይቻለው መንገድ ነፍሳችንን ያስደስታታል። ጸሎትን ቸል ስንል እራሳችንን እና የምንወዳቸውን ሰዎች ቸል እንላለን። በየቀኑ እንዲያጸናን እና እንዲያበረታታን በመፍቀድ ከእግዚአብሔር ጋር ጊዜ እናሳልፍ።
በእርሱ መገኘት እኛን ማርካት እና ማስደሰት ይወዳል። እሱን እንዲያውቁት እና በእሱ እንዲደሰቱ ከእርስዎ ጋር መሆን ይፈልጋል።
በዕለታዊ እንቅስቃሴዎ ለእግዚአብሔር ጊዜ ይመድቡ፣ አለበለዚያ ለእሱ የሚሆን ጊዜ ያጣሉ። ለመጸለይ ችላ ቢሉ ተስፋ ይቆርጣሉ፣ ብቸኝነት ይሰማዎታል፣ እንዲሁም ወደ ክፋት ይወድቃሉ። በትጋት ለመጸለይ ታማኝ ከሆኑ ግን እግዚአብሔር ከሚያስቡት በላይ በከፍተኛ ጥልቀት ይሸልምዎታል።
እግዚአብሔር ለእርስዎ እንደሚጸልይ ያውቁ ነበር?
ጠለቅ ይበሉ
በሚከተሉት መንገዶች ለአምስት ደቂቃ ያህል ይጸልዩ:- ውዳሴ፤ መናዘዝ፤ አንድ መዝሙር ያንብቡ፤ ምስጋና፤ አምልኮ፤ እንዲነጋግርዎ እሱን ይጠብቁት፤ ልመናዎን ለእግዚአብሔር ያካፍሉ፤ ለሌሎች ይጸልዩ፤ መዝሙር 23ን ወይም ሌላ ለጸሎት የሚመች መዝሙር ይጸልዩ፤ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ያሰላስሉ፤ እንደ እሱ ለመሆን እንዲያጸናዎ ይጠይቁት፤ ከዚያም ተጨማሪ ውዳሴ በማቅረብ ይጨርሱ።