ክፍለ ጊዜ 6
ጉዞዎን ከኢየሱስ ጋር ጀምረው ከሆነ ከእርስዎ ጋር እንደሆነ ይመኑ፣ ምክንያቱም በቅርቡ ተስፋ ይቆርጣሉ።
ተስፋ ሲቆርጡ እግዚአብሔር ከድክመትዎ ጨምሮ ከሁሉም ነገር የበለጠ ኃያል መሆኑን ያስታውሱ። እሱ ሕይወትዎን እየቀየረ እና እርስዎን እያደሰ እንደሆነ ይመኑ።
ሲሳነን እና ተስፋ የለሽ እንደሆንን ለማመን ስንፈተን የምናድገው እኛ መልካም ስለሆንን (አይደለንም) ሳይሆን በእሱ ላይ ባለን እምነት እና እሱን ለመውደድ፣ ከፍ ከፍ ለማድረግ እና ለመታዘዝ በምናደርጋቸው ሙከራዎች አማካኝነት ክርስቶስ እኛ ውስጥ ስለሚሰራ ነው።
ኢየሱስ አሁኑኑ በክፋት ከምንወስነው ውሳኔ ሊጠብቀን የሚያስችለው ኃይል አለውን? በርግጥ አለው! በሕይወታችን ውስጥ ያለ እያንዳንዱ መልካም ነገር ሁሉ የሚመጣው ከእሱ ነው። በእምነታችን፣ በፍቅራችን፣ እና በትጋታችን አማካኝነት እኛ ውስጥ ሲሰራ የእኛ መልካም ባህርይ አቅም የሚያገኘው በእሱ ነው።
እናስ እሱ ከክፉ ነገር እንደሚጠብቅዎ የታመነ ነውን? ጥርጥር የለውም!
ታዲያ ለምንድን ነው አቅም የለሽ የምንሆነው? ምክንያቱም በእሱ እንድንተማመን ድካም እንዲሰማን ስለሚያደርግ ነው። ድክመትዎ እንዳያታልልዎ አይፍቀዱ። ይልቁንም እግዚአብሔር ጥንካሬዎ እንደሆነ እንዲያምኑ ምክንያት ያድርጉት።
ታዲያ በእግዚአብሔር ላይ ያለንን እምነት የሚወስድብን ምንድን ነው? ለመታዘዝ ጥንካሬ እንዳለን በድንገት ስንጠራጠር ምን ተቀየረ?
እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ረሳን። በእሱ ውስጥ እኛ ማን እንደሆንን ረሳን። እኛን ክፉ ነገርን ከመምረጥ ለመጠበቅ የሚያስችለው ኃይል እንዳለው ያለን እምነት ላይ ወላውለናል። እናም በእውነት ልባችን ከእሱ ወደሌሎች ነገሮች እንዲርቅ አድርገናል።
የመጨረሻው ስሕተት እጅግ በጣም ተንኮለኛው እና ጎጂው ነው። እያንዳንዱ ክፉ ስሕተት የሚጀምረው ልባችን ከኢየሱስ እንዲርቅ በመፍቀድ ነው። ለዚህ ነው በየቀኑ መጽሐፍ ቅዱስ የማንበብ፣ የመጸለይ፣ እና የማምለክ ልማድን በጽናት ማሳደግ በጣም ወሳኝ የሚሆነው፡፡ ምክንያቱም ትኩረታችን በቀላሉ ይሰረቃል እንዲሁም ትውስታዎቻችንም የአጭር ጊዜ ናቸው።
እግዚአብሔር ሕይወታችን እንደሆነ መቸም ቢሆን መርሳት አንችልም። የመዳን ግጥሙ "ህይወቴን ለውጠህ አዲስ አርገው" የሚል ቃል ይጠቀማል። እሱም ክርስቶስን ካወቅን በኋላ ሕይወታችን ፈጽሞ ከበፊቱ ጋር አንድ እንደማይሆን እውቅና ይሰጣል፣ ምክንያቱ ደግሞ መቶ በመቶ እሱ በመሆኑ ነው።
በጣም የሚወዱት ጓደኛ ወይም የቤተሰብ አባል አልዎት? ለምን ይወዷቸዋል? እርስዎ መልካም ሰው ስለሆኑ ነው?
አንድ ጊዜ ላይ፣ አንድ ሰው አንድን ሰውዬ ሚስቱን የሚወዳት እሱ መልካም ሰው ስለሆነ እንደሆነ ይጠይቀዋል። ይህ ሰውዬውን ግር አሰኘው አስቀየመውም። ድንቅ ስለነበረች ነበር የሚወዳት! ለእሷ ያለው ፍቅር እሱ መልካም ሰው ከመሆኑ ወይ ካለመሆኑ ጋር ምንም የሚያገናኝ ነገር አልነበረውም። እንዲያውም እሱ መልካም እንዳልነበረ ያውቅ ነበር፣ አብልጦ የሚወዳት የእሱ መልካምነትን ማጣት ሳያግዳት ስለምትወደው ነበር።
ለኢየሱስ ያለን ፍቅር ልክ እንደዚያ ነው። ምን ያህል መልካም ከመሆናችን ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም። የምንወደው ድንቅ ስለሆነ ነው። በየቀኑ የእሱ ፍቅር እስከ አጥንታችን ዘልቆ እስከሚሰማን ድረስ ስለ ድንቅ ባህርያቱ ማሰብ አለብን።
ይህንን ኮትኩተው የሚያሳድጉ ሦስት ልምምዶች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ፣ መጸለይ፣ እና ማምለክ ናቸው።
ይህ እንደሚሰራ ይጠራጠራሉ?
ፈጽሞ እንደማይተዎት ወይም እንደማይጥልዎት እግዚአብሔር የገባቸውን ቃላት ያንብቡ። በእርስዎ ላይ መስራት የጀመረውን መልካም ሥራ እንደሚያጠናቅቅ። ሲጠሉት እንደሚወድዎት እና የእርሱ እንዲሆኑ እንደመረጥዎት። ከእርስዎ እምነት ማጣት እና ሆን ብለው ከሚፈጸሙት ክፋት ውጪ እርስዎን ከእርሱ ፍቅር ምንም ነገር እንደማይለይዎት፣ እና እሱ ይቅር እንዳለዎት እና እንደተቀበልዎት።
አእምሮዎን እያደሰ እንደሆነ ሲጠራጠሩ ይህንን የሚያደርገው በቃሉ እንደሆነ እራስዎን ያስታውሱ። ክፉ ነገርን እምቢ ለማለት ኃይል እንዳልዎት ሲጠራጠሩ፣ ቀደም ሲል ክፉ ነገርን ለማሸነፍ ለእርስዎ ብርታት የሰጠበትን ጊዜ እራስዎን ያስታውሱ። እርሱን መውደድ እንደሚችሉ ሲጠራጠሩ፣[24] እሱ እጅግ ድንቅ በመሆኑ አለመውደድ እንደማይቻል እራስዎን ያስታውሱ። መልካም የሆነ ነገር ማድረግ እንደሚችሉ ሲጠራጠሩ፣ በሕይወትዎ ውስጥ ያለ እያንዳንዱ መልካም ነገር ከእሱ የመጣ እንደሆነ እራስዎን ያስታውሱ።
ክርስቶስ እየቀየርዎት እና ሳያቋርጥ አዲስ እያደረገዎት እንደሆነ በማመን በትሕትና፣ በፍቅር እና ለእሱ በተግባር በመታዘዝ ይጓዙ።
የእግዚአብሔር መንፈስ ምናልባት ልናስተውለው በማንችልበት መንገድ እኛን በፍቅር በመቀየር ውስጣችን ይኖራል። የእሱን ሕይወት የምንጋራው ልክ ያልተወለደ ህፃን የእናቱን ደም እንደሚጋራው ነው። ህፃኑ እና እናቱ የተለያዩ ሰዎች ናቸው፣ ሕይወታቸው ግን ውብ በሆነ መንገድ የተዋሃደ ነው። በተመሳሳይ መንገድ ቅዱስ መንፈስ መንፈሳችንን ሕይወት የሚዘራው በኢየሱስ ደም ነው።
ስንጸልይ እና ስናመልከው ውስጣችን የሚሰማን ነገር የእርሱ መንፈስ ነው። የእሱ መንፈስ በውስጣችን መኖሩን ማወቃችን አስፈላጊ የሆነ የዕለት ተዕለት ተሞክሮ ነው። የእሱ መንፈስ በውስጣችን መኖሩን በቋሚነት ካላወቅን እንደክማለን። ከእሱ ጋር ስንሆን ግን መንፈሱ ሌላ ምንም ነገር ሊያደርገን እንደማይችል አድርጎ ያበረታናል።
ጠለቅ ይበሉ
ሮሜ 12:1-21ን ያንብቡ። ይህ ጥቅስ ሕይወታችንን በእውነተኛ እምነት ለእግዚአብሔር አሳልፈን ስንሰጥ በሕይወታችን የሚመጣውን ለውጥ ያሳያል። መንፈሳዊ መታደስ ምን እንደሚመስል እና ምን ስሜት እንደሚሰጥ አንድ ፍንጭ ይሰጣል። እግዚአብሔር እርስዎን እንዴት እያደስዎት እንደሆነ ይጻፉ ያጋሩ። አሁን እሱ የበለጠ እየሰራ ያለው ምን ላይ ነው? እሱ እርስዎን እንዴት በእድገትና ብስለት ጎዳና ላይ በትዕግስት እያስጓዝዎት እንደሆነ አስመልክቶ ሐሳብዎን ይስጡ። እሱ ለእርስዎ ቸር መሆኑን ማረጋገጫ ማየት ይችላሉ?