ክፍለ ጊዜ 10
ቤተ ክርስትያን በእግዚአብሔር የዳነ ማንኛውም ሰው ነው። ቤተ ክርስትያን እኛ ነን።
"ቤተ ክርስትያንን አንፈልግም" ካልን፣ እያልን ያለነው "ሌሎች ክርስትያኖችን እንፈልግም፣ እኛ ራሳችንም ክርስትያን መሆን አያስፈልገንም" ነው።
የእግዚአብሔር ቤተሰብ ነን። የዚህን ቤተሰብ አካል መሆን የክርስትያን ሕይወትን ለመኖር ያግዛል። እያንዳንዳችን ከሌለን ቤተሰብ ስለማይኖር እያንዳንዳችን እናስፈልጋለን። እያንዳንዳችን በፍቅር ካልተደጋገፍን እንበታተናለን። እግዚአብሔር የፈጠረን ከእሱ ጋር
ከእሳቱ እንደወጣው ከሰል ለብቻችን ከሆንን እሳታችን ይጠፋል። ልባቸው በጥልቅ ፍቅር ከሚንቀለቀል ሌሎች ክርስትያኖች ዙርያ ከሆንን ግን ነበልባላችን ይበልጥ ያበራል።
መጽሐፍ ቅዱስ አብሮ መሰብሰብን ችላ እንዳንልም ይነግረናል። ከሌሎች አማኞች ጋር አዘውትረው ካልተገናኙ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ፣ ለመጸለይ፣ እና እርስ በርሳችሁ በክርስቲያናዊ ሕይወት እንድትኖሩ ካልተበረታታችሁ በመጨረሻ ከእግዚአብሔር ርቀው ይወድቃሉ። በዚህ መንገድ ከሌሎች ክርስቲያኖች ጋር መሆናችን እንድናድግ ይረዳናል፤ እኛንም ያበረታታል እና ያስደስተናል። ከተፈጥሯዊ የራስ ወዳድነት ባህሪያችን ያወጣናል።
እርስ በርሳችን የምንገናኘው የግድ ስለሆነ ብቻ አይደለም። እርስ በርስ የምንገናኘው አንድ ላይ መሆን ስጦታ ስለሆነ ነው። በክርስትያን ጓደኞቻችን ቤት መገናኘት ውብ እና ጠቃሚ ቢሆንም እዚያ መገናኘት አለብን ማለት አይደለም። ከዚያ በላይ ያስፈልገናል።
የምንፈልገው ነገር በእርግጥ ምንድን ነው?
ወዳጅ ጓደኞች፣ የግል ተጠያቂነት፣ ጠንካራ ትምህርት፣ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ስልጣን እና ሌሎች ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዲቀርቡ የመምራት ዕድሎች ያስፈልጉናል።
እምነታቸውን በአኗኗር ዘይቤያቸው ካረጋገጡ እና እግዚአብሔርንና ቃሉን በደንብ ካወቁ በኋላ ሥልጣን በተሰጣቸው ፓስተሮች እና ሽማግሌዎች መመሪያ ስር መኖር ያስፈልገናል። የሚሰብኩትን በሚኖሩት ብቁ መምህራን ሥልጣን ስር ካልሆንን፣ ስለ እግዚአብሔር ያለን እምነት እግዚአብሔር በፍጹም ወዳላሰበው ነገር ሊቀየር ይችላል።
ብዙ ሰዎች ሌሎች ሰዎች በተወሰነ የአኗኗር መንገድ እንዲኖሩ ተጠያቂ እንዲያደርጓቸው አይወዱም። ሕይወታችን እንዲመረመር እና ነገሮችን እያበላሸን እንደሆነና መቀየር እንዳለብን እንዲነገረን ምቾት አይሰጥም። ተጠያቂ ካልሆንን ግን፣ ስህተቶቻችን ፈንድተው ሰዎችን እስከሚጎዱበት ደረጃ ድረስ ሊከማቹ ይችላሉ።
የቤተ ክርስቲያን አካል በመሆን፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸውን በሚመስሉ ብቁ አስተማሪዎች ሥር፣ ራሳችንን ተጠያቂ እናደርጋለን።
በተጨማሪ የብቁ መምህራን ሥልጣን ሌሎች ሰዎችን ማበላሸት ከሚፈልጉ ሰዎች ይጠብቀናል። ከተበደልን ለእገዛ የምንሄድባቸው ሰዎችን ይሰጠናል። ብዙውን ጊዜ የሚደግፈን ሰው ያስፈልገናል።
በመጨረሻ፣ ይህ ሌሎች ሰዎች ወደ ክርስቶስ እንዲቀርቡ የምንረዳበትን መንገድ ለምናገኝበት ማሕበረሰብ ቅርጽ ይሰጠዋል። እግዚአብሔር ሕይወታችንን ከቀየረ በኋላ ስለእርሱ ለሌሎች እንድናስተምር የነገረንን መርሳት አንችልም።
ቅርጽ አልባ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ወንጌልን መስበክ ቀላል ነው፣ ሰዎችን ደቀ መዝሙር ማድረግ ግን የረጅም ጊዜ ቁርጠኝነት ነው። ሰዎችን በስሕተት ከመምራት ወይም ልናግዛቸው የምንሞክራቸውን ሰዎች ከመጉዳት ሊጠብቁን ለሚችሉ ፓስተሮች እና ሽማግሌዎች ስልጣን እራሳችንን እያስገዛን ሁልጊዜ ሰዎችን ደቀ መዝሙር ማድረግ አለብን።
የአማኞች ህብረትን እንዴት ያገኛሉ? መጀመሪያ፣ እግዚአብሔር እንዲረዳዎት ይጠይቁ። ከዚያ በዙሪያዎ ይጠይቁ። በንጽሕና የሚኖሩ፣ አፍቃሪ ሰዎችን ያስተውሉና የት ቤተ ክርስትያን እንደሚታደሙ ያጣሩ። ቤተ ክርስትያናትን መጎብኘት ይጀምሩ። ሰዎችን ተቀባይ፣ እውነተኛ፣ እና አፍቃሪ የሆኑ ሰዎች ያሉበትን ቤተ ክርስትያን ይፈልጉ። መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ የሚያስተምረውን የሚያምኑ እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚናገረውን የማይጠራጠሩ ፓስተሮችንና ሽማግሌዎችን ይፈልጉ። እናምንበታለን የሚሉትን ነገር የሚኖሩ መሆናቸውንም ያረጋግጡ። ካልሆነ ግን እነሱ በእርግጥ አያምኑትም።
ወደየትኛውም ቤተ ክርስትያን ይሂዱ፣ ሰዎቹ እርስ በርሳቸው ይዋደዳሉ እንዲሁም ያገለግላሉ? መጽሐፍ ቅዱስን የሚወዱ እና ሊዳስሱትና ሊያዩት በሚችሉት ልክ እምነታቸውን ተግባራዊና እውነተኛ በሆነ መንገድ ለመኖር እርስ በርስ የሚረዳዱ ናቸው? ማንም ሰው ፍጹም አይሆንም! ነገር ግን እርስዎ ሕይወታቸው ወጥነት ያለው ይሁን አይሁን ግድ በማይሰጣቸው እና በስህተታቸው በሚጸጸቱ ሰዎች መካከል ያለን ልዩነት ማወቅ ይችላሉ።
እስኪ ራስዎን ይህንን ጥያቄ ይጠይቁ? እዛ ቦታ እግዚአብሔር እየተመለከ እና እየተከበረ ነው?
ፍጹም ሰዎች እንደሌሉ ሁሉ ፍጹም የቤተ ክርስትያን ማሕበረሰብ የለም። በቃ ጥሩ ቤተ ክርስትያን ያግኙ፣ በቋሚነት ይሂዱ እንዲሁም አያማርሩ። ማየት የሚፈልጉትን ለውጥ ያድርጉ። ቤተሰብዎን በክርስቶስ ለማበረታታት አጋጣሚዎችን ይፈልጉ። ሰዎችን ከልብ ይውደዱ! ከንጹሕ ልብ በመነጨ ፍቅርዎ ያገልግሉ። በሌሎች ሰዎች ዘንድ "መልካም" መስሎ ለመታየት በመሞከር አይደለም።
የሰው ልጆች መሆናችን እና እርስ በርሳችን እንደምናስፈልግ ይገንዘቡ። እርስዎ በጭራሽ አያውቁም፣ ግን የሚያበሳጭዎት ሰው እርስዎ እንዲያድጉ እግዚአብሔር ወደ ሕይወትዎ ያስገባው ሰው ሊሆን ይችላል። እርስዎም ወደ ሕይወታቸው የገቡት በክርስቶስ አንዲያድጉ በደግነት እንዲረዱዋቸው ሊሆን ይችላል። በሰላም ኑሩ እንዲሁም እግዚአብሔርን በጋራ ከፍ ከፍ አድርጉ። ያ ነው ቤተ ክርስትያን።
ጠለቅ ይበሉ
ቤተ ክርስትያን ያግኙና በመጪው እሑድ ይታደሙ። ተሞክሮው ላይ ያልዎትን ሐሳብ እና እንዴት ስሜታዊ፣ መንፈሳዊ፣ እና አካላዊ ተጽእኖ እንደፈጠረብዎ ይጻፉ።